
ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ችግኝ መትከል የመልካም ትውልድ መገለጫ ነው” ሲሉ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
የተቋሙ እና በስሩ ያሉ ተቋማት ሰራተኞችና አመራሮች በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል መርሃ-ግብር ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ግቢ እያኖሩ ነው።
እየተተከሉ ያሉት ችግኞች ለምግብነት የሚውሉ መሆናቸው ተገልጿል።
“ዛፎችን መትከል የመልካም ትውልድ መገለጫ ነው፤ ተንከባክቦ እንዲጸድቁ ማድረግ ከዚህ የላቀ ፋይዳ ያለው ነው” ብለዋል አቶ ተመስገን ባስተላለፉት መልዕክት።
በዓለም ላይ የሚደርሱ የተፈጥሮ አደጋዎች በአብዛኛው የሚከሰቱት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው ያሉት ዳይሬክተር ጀነራሉ ይህንንም ለመከላከል ችግኞችን መትከል ጉልህ አበርክቶ እንዳለው አመልክተዋል።
ችግኞቹ ለታለመለት አላማ እንዲውሉ ለማድረግም የእንክብካቤ ሥራው በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
