
ጅማ: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በጅማ ዞን በዚህ ዓመት 336 ሚሊዮን ችግኝ እንደሚተከል ተገልጿል።
ዛሬ በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርም በጅማ ከተማ እና ማና ወረዳ 32 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኞች እየተተከሉ ይገኛሉ።
የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ ሥራው በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን አሥተዳደር ነዎሪዎች እየተካሄደ ነው የሚገኘው። ነዋሪዎቹ በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ችግኞችን እየተከሉም ይገኛሉ።
በዞኑ በተለያዩ አከባቢዎች የችግኝ ተከላው ቀኑን በሙሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው የተባለው።
በሥፍራው የኢንሳ ዋና ዳሬክተር ሰለሞን ሰኮሩ ተገኝተው ችግኝ ተክለዋል፡፡
ዋና ዳሬክተሩ እንደገለጹት:-
🌱🌱 ዛሬ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን እንትከል በሚል መርህ እየተካሔደ ባለው መርሐ ግብር ከጠዋት ጀምሮ የጅማ ዞን ነዋሪዎች ያሳያችሁት ርብርብ ይደነቃል።
🌱🌱 ዛሬና ከዚህ በፊትም የተተከሉ ችግኞችን እንደ ልጆቻችሁ ተንከባክባችሁ አሳድጉ ብለዋል።
ዘጋቢ፡- አየለ መስፍን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
