
ጎንደር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በ15 ሺህ የችግኝ ጣቢያዎች 118 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኞች መዘጋጀታቸውን የግብርና መምሪያው የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ ሙሉቀን ተፈራ ገልጸዋል።
“በአንድ ጀምበር በዛሬው ዕለት 24 ሚሊዮን ችግኞች ይተክላሉ” ያሉት አቶ ሙሉቀን በአንድ ጀንበር የተከላ መርሐ ግብር በዞኑ 500 ሺህ የሠው ኃይል እየተሳተፈ ነው ብለዋል። እየተተከሉ ከሚገኙት ችግኞችም 51 ነጥብ 5 በመቶ ሀገር በቀል እፅዋት መኾናቸውን ቡድን መሪው ጠቅሰዋል።
በአንድ ጀምበር እየተተከሉ ከሚገኙት ችግኞች ከ3 ሚሊዮን በላይ የደን ፣ ከ45 ሺህ በላይ የፍራፍሬ እና ከ5ሺህ 500 በላይ ለከተማ ውበት የሚያገለግሉ ችግኞች መኾናቸውን ግብርና መምሪያው አስታውቋል።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ጭንጫዬ ቀበሌ የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አቶ ወርቁ ኃይለማርያምን ጨምሮ ኀብረተሰቡ በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡- አገኘሁ አበባው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
