“የዛሬው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብራችን የይቻላል ማሳያ ነው” አሕመድ ሽዴ

51

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምብር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአማራ ክልል የፌደራልና የክልል ከፍተኛ መሪዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሸዴ በሀገር ደረጃ የሚካሄደውን በአንድ ጀንበር የ500 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዘመቻ ለመሳተፍ በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ ተገኝተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የዛሬው የ500 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር የመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የይቻላል ማሳያ ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት ለሀገራዊ ጉዳዮቻችን በአንድነትና በቁርጠኝነት ከተሰለፍን የኢትዮጵያን አንድነት ፣ እድገት እና ሰላሟን ማጽናት እንደምንችል ማሳያ ነው ብለዋል።

በአማራ ክልል ለሀገራዊ አጀንዳው የተደረገው ዝግጅት የተናበበና የሚደንቅ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ። ክልሉ ሀገራዊ ተልእኮውን ለመወጣት ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ርብርብና ተሳትፎ የሚያስመሰግን ነውም ብለዋል።

በክልሉ የት ቦታ ላይ ምን እየተከናወነ እንደኾነ ለማሳወቅ በዲጂታል ካርታ የመረጃ ልውውጥ መካሄዱ ዘመቻው በትክክለኛ መንገድ እየተተገበረ ስለመኾኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

ለአረንጓዴ አሻራው የክልሉ መንግሥት፣ ግብርና ቢሮ እና የክልሉ ካቢኔ ያደረገውን ጠንካራ ዝግጅትና ትግበራም አመሥግነዋል።

ዘጋቢ:- ጋሻው አደመ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል እስከ ጠዋቱ 4 ሰዓት 105 ሚሊየን 152 ሺ 813 ችግኞች ተተክለዋል።
Next article“በአንድ ጀምበር 24 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ ” የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ