በአማራ ክልል እስከ ጠዋቱ 4 ሰዓት 105 ሚሊየን 152 ሺ 813 ችግኞች ተተክለዋል።

67

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በአንድ ጀንበር 260 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር በሁሉም ዞኖች በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ከንጋት ጀምሮ እየተከናወነ የሚገኘው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በ 128 ወረዳዎች፣ በ 1690 ቀበሌዎች እየተከናወነ ነው።

እስከ ጠዋቱ 4 ሰዓትም 12 ሺ 148 ሄክታር መሬት በችግኝ የተሸፈነ ሲሆን 105 ሚሊየን 152 ሺ 813 ችግኞች ተተክለዋል።

በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሳታፊ ወንድ 1 ሚሊየን 408 ሺ 462 ሴት እና 565 ሺ 549 በድምሩ 1 ሚሊየን 974 ሺ 11 ሰዎች ተሳትፈውበታል።

መረጃው የአማራ ኮሙኒኬሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ የክልሉ አረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም በጅግጅጋ አስጀምሩ።
Next article“የዛሬው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብራችን የይቻላል ማሳያ ነው” አሕመድ ሽዴ