የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ የክልሉ አረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም በጅግጅጋ አስጀምሩ።

41

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ ከኢፌዴሪ ውሃና ኤነርጂ ሚንስትሩ ኢ/ር ሀምታሙ ኢተፋ (ዶ.ር) የተመራ የፌደራል ልዑክ ጋር በመሆን በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የሚጀምርበት ፕሮግራም በጅግጅጋ አስጀምረዋል።

በመርሃግብሩ ላይም የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሁሴን ቃሲም (ዶ.ር) የኢፌዴሪ ውኃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ኢር ሀምታሙ ኢተፋ (ዶ.ር) ፣ የገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ.ር) ፣የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ደዲሳ፣ በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌና ሌሎች የክልልና የፌዴራል ሥራ ኃላፊዎችና የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል። መረጃው የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኀብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ቁርጠንነቱን አሳይቷል” አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ
Next articleበአማራ ክልል እስከ ጠዋቱ 4 ሰዓት 105 ሚሊየን 152 ሺ 813 ችግኞች ተተክለዋል።