“ኀብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ቁርጠንነቱን አሳይቷል” አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ

29

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በአማራ ክልል እየተካሄደ ነው፡፡ በመርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ በአንደኛው ዙር ያገኘናቸውን ትልልቅ ድሎች ወደ ከፍተኛ ጥቅም ለማሻገር አስተዋጽዖ ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

ሀገራችን ለረጅም ጊዜ አጋጥሟት የነበረውን የደን መራቆት ወደ ነበረበት ለመመለስ በሚደረገው እንቅስቃሴ የታሪኩ ተሳታፊ በመኾናችን ደስ ብሎናል ብለዋል፡፡ ኀብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር፣ በሀገር ደረጃ የተነደፉ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ ለማድረግ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል ነው ያሉት በመልዕክታቸው፡፡በሚኖረው ታሪካዊ ሽግግር የሚኖረው አበርክቶ ታላቅ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ የክልሉ መንግሥትና ሕዝብ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ ለአረንጓዴ አሻራው ባለቤቱ ሕዝብ መኾኑን ያነሱት አፈ ጉባኤዋ ችግኞቹ ጸድቀው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ሁሉም የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“እስከ ረፋዱ 3 ሰዓት ባለው የተከላ መርሐ ግብር 147 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ተችሏል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ
Next articleየሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ የክልሉ አረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም በጅግጅጋ አስጀምሩ።