“እስከ ረፋዱ 3 ሰዓት ባለው የተከላ መርሐ ግብር 147 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ተችሏል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ

16

አዲስ አበባ: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ እንዳሉት፡-

👉 ዛሬ በመላ ሀገሪቱ እየተከናወኑ የሚገኙ ተከላዎች በ9 ሺህ የመትከያ ስፍራዎች ላይ ነው።

👉 ዛሬ እየተካሔደ በሚገኘው መርሐ ግብር ላይ 34 ሚሊዮን ዜጎች እየተሳተፉ ነው።

👉 የዛሬ 3 ዓመት በአንድ ጀምበር 20 ሚሊዮን ዜጎች ተሳትፈው በአንድ ጀንበር መትከል የታቀደውን ችግኝ መትከል ተችሎ ነበር ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡

👉 ዛሬ 500 ሚሊዮን ችግኝ ይተከላል ተብሎም ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአረንጓዴ አሻራ አብሮነትን እና አንድነትን የሚያጠናከር ነው” ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ
Next article“ኀብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ቁርጠንነቱን አሳይቷል” አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ