
አዲስ አበባ: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በአለርት ሆስፒታል 35 ሺህ ችግኞችን እየተከሉ ይገኛሉ።
በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በተጀመረዉ መርሐ ግብር የጤና ሚኒስቴር ከኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ነዋሪዎች ጋር በመኾን የችግኝ ተከላዉ እየተከናወነ ነዉ።
የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ “ዛፍ ማለት ህክምና ነዉ፤ ዛፍ ከሌለ ህክምና የለም ይህ መርሐ ግብር ይህንን የምናሳይበት ነዉ” ብለዋል።
ዛፍ ስንተክል ለነገ ትዉልድ ጥሩ የአየር ንብረት ማቆየት እንደኾነ አስገንዝበዋል፡፡
በዚህ የችግኝ ተከላ የተሳተፋችሁ ነዋሪዎች ታሪክ በማስቀመጣችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
በችግኝ ተከላዉ የተሳተፉ የሆስፒታሉ ሠራተኞች እና የአካባቢዉ ነዋሪዎሽ የዚህ ታሪካዊ ቀን ተሳታፊ በመኾናቸው የተሰማቸዉን ደስታ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
