
አዲስ አበባ: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አዲስ አበባ 500 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር የመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሐ ግብሩ ባስታለለፉት መልእክት እንደ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ተምሳሌትነታችንን ከፍ ባደረገ መንገድ ከ4 ሚሊዮን ችግኝ በላይ በ140 ቦታዎች ላይ እንተክላለን ነው ያሉት፡፡
ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገ ምግባችን፣ የዛሬን የምንተክለው ችግኝ ነገ በአየር ንብረት ለውጥ የሚመጣውን በሽታ መከላከያ መድኃኒታችን ነው፣ የዛሬ የምንተክለው ችግኝ በአየር መዛባት ምክንያት የሚመጣውን አደጋ መከላከያ ጋሻችን ነው፣ የነገ ጥላ ከላላችን ነው፣ የነገ ውበት መወዳደሪያ አቅማችን ነው፣ ዛሬ የምንተክለው ችግኝ ኢትዮጵያውያን አንድነታችንን የምናሳይበት ትልቅ መድረክ ነው፣ ከተባበርን ምን ልንሠራ እንድምንችል ለዓለም የምናሳየውና የምንናገርበት ቋንቋችን ነው ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
