ዛሬ በኅብረት እያከናወንን ያለው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ የሚያሳየው በኅብረት ሁሉንም ማድረግ እንደምንችል ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።

50

አዲስ አበባ: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በክልሉ ዑራ ወረዳ ቤልሚሊ ቀበሌ በማለዳው የተጀመረው የችግኝ ተከላን ያስጀመሩት ርዕሰ መሥተዳድሩ “ይህ ታሪክ የምንሠራበት ቀን ነው፤ የክልላችንን የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ የሚደግፍ አሻራችንን የምናስቀምጥበት ዕለት ነው“ ብለዋል።

የአየር ንብረት እንዳይዛባ እና ለሰው ልጆች ጥቅም የሚውል የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከሕዝባችን ጋር ኾነን እያካሄድን በመኾኑ ሁላችንንም እንኳን ለዚህ ቀን አበቃን ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ ለሕዳሴው ግድብ ቅርብ ርቀት ከመኾናችን አንጻር ብዙ ድርሻ ስለሚጠበቅብን በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ችግኞችን መትከል እንቀጥላለን፤ እናሳካዋለንም ነው ያሉት።

የችግኝ ተከላ ላይ ያሳየነውን ቁርጠኝነትና ኅብረት በሌሎች የመልካም አሥተዳደር እና የብልጽግና ጉዞዎች መድገም እንደምንችል አንጠራጠርም ብለል ርዕሰ መሥተዳድሩ።

ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋርም ርዕሰ መሥተዳድሩ ችግኝ ተክለዋል። በመርሐ ግብሩ የፌዴራልና የክልል የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም ሌሎች የኅረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል። መርሐ ግብሩ እስከ ጀምበር መግቢያ ይቀጥላል።

ዘጋቢ፡- ድልነሳ መንግሥቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጅማ ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ ከማለዳው ጀምሮ ችግኞችን እየተከሉ ይገኛሉ።
Next article“ዛሬ የምንተክለው ችግኝ ኢትዮጵያውያን አንድነታችንን የምናሳይበት ትልቅ መድረክ ነው”