በጎንደር ከተማ አሥተዳደር በሁሉም ቀበሌዎች ችግኝ ተከላ እየተካሄደ ነው።

64

ጎንደር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በችግኝ መትከል መርሐ ግብር የተሳተፉ የሥራ ኀላፊዎች እና የከተማው ነዋሪዎች መትክል ብቻ ሳይኾን ከተከሉ በኋላም ችግኞችን መንከባከብ ያስፈልጋል ብለዋል።

በችግኝ መትከል መርሐ ግብሩ የተሳተፉ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደምም ችገኞችን መተከላቸውን እና የተከሏቸውንም ችግኞች ሲንከባከቡ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

የጎንደር ከተማ ግብርና መምሪያ ኀላፊ አክናፍ አለሙ በተያዘው ዓመት 4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል እየተሠራ ሲሆን ከዚህም 200 ሺህ የሚሆነው አትክልት እና ፍራፍሬ መኾኑን ገልጸዋል።

ያለፈው ዓመት ከተተከለው ችግኝ 78 ከመቶ የሚኾነው በሚደረገው ክትትል መጽደቅ መቻሉን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩ አቡሃይ ገልጸዋል።

በቀጣይም የቁጥጥር ሥራውን በማሳደግ የጽድቀት መጠኑ ከፍ እንዲል እንሠራለን ብለዋል።

ዘጋቢ:- ዳንኤል ወርቄ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ ጠለምት ወረዳ ዞናዊ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እየተካሄደ ነው።
Next articleየብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ አረንጓዴ አሻራቸውን ለማሳረፍ ባሕር ዳር ገብተዋል።