“እኛ ኢትዮጵያውያን ማሸነፍ ሥራችን ነው” ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር

83

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በሐዋሳ ተገኝተው በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ ችግኝ ተክለዋል፡፡

ሚኒስትሯ ባስተላለፉት መልእክት የውስጣችን አንድነት በማውጣት፣ በምንም አይነት የፖለቲካ ልዩነት ሳንገደብ ከሠራን፣ አሻራችንን ካሳረፍን፣ ከድኅነት ጋር ትግል ማድረግ ብቻ ሳይኾን ማሸነፍ እንደምንችል የዛሬዋ ቀን ማሳያ ናት ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ድንበር ተነክቷል ሲባል ከዳር እስከዳር እንደ ንብ እንደሚነሱ ያስታወሱት ሚኒስትሯ እንደ ንብ ተናድፎ መቀመጥ ሳይኾን በዛው መንፈስ ድኅነትን ማሸነፍና መቅበር ይገባል ነው ያሉት፡፡

ዛሬ ለነገው ትውልድ ታሪካችን የምናሳርፍበት ነው፣ መትከል ብቻ ሳይኾን ለመንከባከብ ኀላፊነት መውሰድ ይገባናልም ብለዋል፡፡

ሁላችን ኀላፊነታችንን ከተወጣን ኢትዮጵያን እንድ እርምጃ እናራምዳለን ነው ያሉት፡፡

ሁሉም በያለበት አሻራውን ያሳርፍ፣ ለራሳችን ብቻ ሳይኾን ለነገ ትውልድ እንትረፍ፣ ዛሬ እኛ ቆመን መናገር የቻልነው ትናንት አባቶቻችን ተክለው ባቆዩን ጥላ ስር ነው ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን መሸነፍን አንፈልግም፣ ማሸነፍ ሥራችን ነው፣ በአረንጓዴ ልማት ዘርፍም እናሸንፋለን ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ባለፉት ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የመጣውን ለውጥ ገልጿል።
Next article“የሚያምርብን ስናብር ነው፤ አብሮ ታሪክ መሥራት ከሁሉም በላይ ትልቁ ድል ነው ” አቶ ደመቀ መኮንን