የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ባለፉት ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የመጣውን ለውጥ ገልጿል።

32

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የቢሮው ምክት ኃላፊ ዶክተር አልማዝ ጊዜው የአረንጓዴ አሻራ ልማት እና የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ ባለፉት ዓመታት ከተተገበረ ጀምሮ ያመጣውን ለውጥ ለማረጋገጥ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከምርምር እና ከግብርና ቢሮ ጋር በመቀናጀት ዳሰሳዊ ጥናት ተካሂዷል ብለዋል፡፡

በዚህም፦
👉🏻የክልሉ የደን ሽፋኑን ከነበረበት 14 በመቶ ወደ 16 በመቶ ማደጉን ገማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

👉🏻 እስከ 22 በመቶ የአፈር ክለት ቀንሷል፡፡

👉🏻የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ ጨምሯ፡፡

👉🏻በሀገር በቀል ላሞች ከ1 ሊትር ወደ 2 ሊትር፣ ዝርያቸው በተሻሻሉ እንስሳት ደግሞ 12 ሊትር ወተት በአንድ ላም ማሳደግ ተችሏል።

👉🏻በሰብል ደግሞ በአማካይ በሄክታር ከ2 እስከ 8 ኩንታል የሰብል ምርት ጨምሯ፡፡

👉🏻ለዜጎች የሥራ እድል በመፍጠርም አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

👉🏻ከ140 ሺህ በላይ ዜጎች በንብ ማነብ፣ በማድለብ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በችግኝ ማፍላት፣ ዘር በማባዛት ሥራ ላይ ተሠማርተው እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል ዘመቻ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ዘንዘልማ ቀበሌ ገላድ ተፋሰስ አካባቢ ተጀምሯል።
Next article“እኛ ኢትዮጵያውያን ማሸነፍ ሥራችን ነው” ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር