በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል ዘመቻ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ዘንዘልማ ቀበሌ ገላድ ተፋሰስ አካባቢ ተጀምሯል።

48

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር እየተከናወነ ነው፡፡

ዘመቻው ከጥዋቱ 12 ሠዓት ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተጀመረ ሲሆን ቀኑን ሙሉ የሚቀጥል ነው ተብሏል።

እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ በሚቆየው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 260 ሚሊየን የችግኝ መትከያ ጉድጓድ እንደተዘጋጀም ተጠቅሷል፡፡

26 ሺህ ሄክታር መሬት በችግኝ እንደሚሸፈን እና በዕለቱም 5 ሚሊየን ሕዝብ በችግኝ ተከላው እንደሚሳተፍ ተጠቁሟል፡፡

በክልሉ በአንድ ጀምበር 260 ሚሊየን ችግኝ እንደሚተከል ተመላክቷል።

የከተማው ነዋሪዎች በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ እየተሳተፉ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ችግኞችን በጋራ እንደተከልን ሁሉ ሰላማችንን በጋራ በመጠበቅ ደኅንነቷ የተረጋገጠባት ዲሞክራሲያዊት ሀገር እንገነባለን” ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ
Next articleየአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ባለፉት ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የመጣውን ለውጥ ገልጿል።