ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃግብርን በአዲስ አበባ አስጀመሩ።

98

አዲስ አበባ: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃግብርን በአዲስ አበባ ጉለሌ እፅዋት ማዕከል አስጀምረዋል።
አዲስ አበባ በአንድ ጀንበር ብቻ 4 ሚሊዮን ችግኞችን በ140 ቦታዎች ለመትከል አቅዳ ሥራ መጀመሯን ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል።

800 ሺህ የከተማዋ ነዋሪዎች በችግኝ ተከላ መርሐግብሩ ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዕለቱ ለፍራፍሬና ለከተማ ውበት የሚሆኑ ዘርፈ ብዙ ችግኞች በልዩ ሁኔታ እንደሚተከሉም ተጠቁሟል፡፡
የዛሬው መርሐግብር የአንድነታችን ማሳያ የአብሮነታችን ምልክት ነውም ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ዓለምን እየፈተነ ለሚገኘው የአየር ንብረት ለውጥ ችግር አይነተኛ መፍትሔ መሆኑን አቶ ደመቀ መኮንን ተናግረዋል።
በማስጀመሪያ መርሐግብሩ ላይ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፤ የሃይማኖት አባቶችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በጉለሌ እፅዋት ማዕከል ብቻ በአንድ ቀን 50 ሺህ ችግኞች ይተከላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃው የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ነው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሀረሪ ክልል የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
Next article“ችግኞችን በጋራ እንደተከልን ሁሉ ሰላማችንን በጋራ በመጠበቅ ደኅንነቷ የተረጋገጠባት ዲሞክራሲያዊት ሀገር እንገነባለን” ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ