
ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የችግኝ ተከላ ሁነቶች መከታተያ ክፍል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው።
በእያንዳንዱ የሃገሪቱ ክፍሎች እየተተከሉ ያሉ ችግኞች የደረሱበት ደረጃ መረጃ ይሰበሰብበታል።
ከ9 ሺህ በላይ የሚሆኑ ለችግኝ መትከያነት ከተዘጋጁ ስፍራዎች በቀጥታ በአንድ ግለሰብ መረጃ ወደ ሥርዓቱ ይደርሳል።
የችግኝ መትከያ ስፍራዎች ችግኞችን ከመያዝ አቅማቸው ጋር በጥናት የተለየ በመሆኑ የተሳሳቱ ሪፖርቶች ሊቀርቡ አይችሉም።
በመርሐ ግብሩ ችግሮች ያጋጠሙባቸው አካባቢዎች ካሉም በፍጥነት ችግሩን ለመፍታት ያስችላል።
ባለሙያዎቹ ቁጥራዊ አሃዞችን በቀጥታ እየተከታተሉ ለመገናኛ ብዙሃን ያደርሳሉ።
የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላው አካል ለመሆን ኢትዮጵያውያን ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ወደ ወደ ችግኝ መትከያ ቦታዎች በማምራት የችግኝ ተከላውን እያከናወኑ ይገኛሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
