“ችግኝ መትከላችንን በጠዋት ጀምረናል፤ እስከምሽት ይቀጥላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር)

44

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) ዛሬ ማለዳ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።

ለመላው ኢትዮጵያውያን በማለዳ በዝናብ ወጥታችሁ አረንጓዴ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ ለምትገኙ በሙሉ ምስጋናችን ይድረስ ብለዋል።

ዛሬ ኢትዮጵያውያን በህብረት ታሪክ የምንሰራበት ቀን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ዛሬ ለኛ ቀላል የሚመስለው ጉዳይ ብዙዎች የከበዳቸው እና የማይችሉት ነው ብለዋል።

አክለውም ህጻናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ሴቶች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሃገራቸውን አረንጓዴ አልብሰው ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ መቁረጣቸው ትልቅ መታደል መሆኑን ገልፀዋል።

በጠዋት ጀምረናል፤ እስከምሽት መትከላችን ይቀጥላል፤ በርቱ በዝናብ የቆምነው የተሻለ ሀገር ለመፍጠር ነው ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን እያካሄዱ ነው፡፡
Next articleየአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን ባለሙያዎች በሁነት መከታተያ ክፍል እየተከታተሉ ይገኛሉ።