ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን እያካሄዱ ነው፡፡

67

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጵያ 500 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ተክላ በዓለም ፊት የራሷን ክብረ ወሰን ለማሻሻል የችግኝ ተከላ መረሐ ግብር በማለዳው ጀምራለች፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማ ከተማ በመገኘት ነው አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩት።

መላው ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን አረንጓዴ ካባ እንዲያለብሱ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የአረንጓዴ አሻራቸውን እያሳረፉ ነው፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውም አረንጓዴ አሻራቸውን እያሳረፉ ነው፡፡
ኢትዮጵያ 25 ቢሊዮን ችግኞችን ተክላ፣ ተጨማሪ 25 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ሁለተኛ ምዕራፍ ጀምራለች፡፡

ዓለምን እየፈተናት የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላል፣ የምጣኔ ሀብት ተጠቃሚ ለመኾን እና ውብ የኾነች ሀገር ለትውልድ ለማቆየት ነው የአረንጓዴ አሻራ እየተከናወነ ያለው፡፡

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ዛሬ ሁሉም ዜጋ የሀገሩን ፍቅር የሚያሳይበት ዕለት ነው” ሚኒስትር ዴዔታ ሠላማዊት ካሳ
Next article“ችግኝ መትከላችንን በጠዋት ጀምረናል፤ እስከምሽት ይቀጥላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር)