“በ15 ትምህርት ቤቶች የ40 ሚሊዮን ብር የማኅበረሰብ አቀፍ ፕሮጀክቶች ትግበራ እየተከናወነ ነው” አልማ ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ

59

ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ልማት ማኅበር ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ በከተማ አስተዳደሩ ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስመርቋል። ለግንባታው ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ወጭ መደረጉን የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ አባተ አውግቸው ተናግረዋል። ግንባታውም ትምህርት ቤቱን ከደረጃ ሁለት ወደ ደረጃ ሶስት ማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት። የማኅበረሰቡ ተሳትፎ በገንዘብ ሲሰላ ከ159 ሺህ ብር በላይ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

240 ወንበሮች የመማር ማስተማሩን ሥራ ለማስጀመር እንደሞሟሉም ኀላፊው ተናግረዋል። የትምህርት ቤቱ መገንባትም ምቹ የመማር ማስተማር ሁኔታ ይፈጥራል ያሉት ነዋሪዎቹ የውኃና የመንገድ ችግሮችም ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት በከተማዋ አልማ ከማኅበረሰቡ ጋር በመሆን የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት ከትብብር ብዙ ለውጥ እንደሚገኝ ያረጋገጡ ናቸው ብለዋል። ነዋሪዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች በየደረጃው ምላሽ እንደሚያገኙም ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል። ጽሕፈት ቤቱ በ15 ትምህርት ቤቶች በ40 ሚሊዮን ብር እየሠራቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች እስከ መጪው ታህሳስ 2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቁም ተመላክቷል።

ዘጋቢ:–ሥነ-ጊዮርጊስ ከበደ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የኅብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ዉኃ አቅርቦት ሽፋንን ለማሳደግ እየሠራን ነው” የምሥራቅ ጎጃም ዞን ውኃ እና ኢነርጂ መምሪያ
Next articleየኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት አረንጓዴ አሻራቸውን እያኖሩ ነው።