ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 84.7 በመቶ 50% እና ከዚያ በላይ በማምጣት ማለፋቸውን አስታወቀ።

129

ባሕር ዳር: ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ79 ፕሮግራሞች 3229 ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 84.7 በመቶ 50% እና በላይ በማምጣት ማለፋቸውን አስታውቋል።

በመደበኛው መርኃ ግብር ብቻ ፈተናውን ከወሰዱ 2843 ተማሪዎች ውስጥ 89.5 በመቶ 50 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ሲሆን ፈተና ከተሰጠባቸው ፕሮግራሞች ውስጥ 32 ፕሮግራሞች 100% (ሁሉም) ተማሪዎች፣ በ14 ፕሮግራሞች ደግሞ በእያንዳንዱ ፕሮግራም አንድ ተማሪ ብቻ ሲቀር ሁሉም አልፈዋል።

በኤክስቴንሽን መርኃ ግብር 45 ተማሪዎች ተፈትነው 55.3%፣ በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር 305 ተማሪዎት ተፈትነው 43.9%፣ በክረምት መርኃ ግብር 34 ተማሪዎች ተፈትነው 85.3% ያሳለፈ ሲሆን በሁሉም መርኃ ግብሮች በአማካይ 84.7% የመውጫ ፈተናውን ማለፋቸው ታውቋል። መረጃው የዩኒቨርሲቲው ነው::

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ማታ ጀምሮ መመልከት ይችላሉ – የትምህርት ሚኒስቴር
Next article“አምሳያ ለሌላት እናት፣ የተዋበውን ካባ አልብሷት”