
ባሕር ዳር: ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስቴር ከሰኔ 30 ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በማጠናቀቅ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ማታ ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ አስታውቋል።
በዚህም ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ እሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ በ https://result .ethernet.edu.et በመግባት ማወቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።
በመውጫ ፈተናው የሚፈለገውን የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ፈተናውን በየስድስት ወሩ ደጋግመው መውሰድ እንደሚችሉም ነው የተገለፀው።
የመውጫ ፈተናው ከመሰጠቱ አስቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎች ከፈተና ሥርዓቱ ጋር እንዲለማመዱ የሙከራ እና የሞዴል ፈተና እንዲወስዱ መደረጉ ይታወሳል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከተጀመሩ ሪፎርሞች አንዱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
