“መንግሥት አማራ ነን እንጅ አማራ እንሁን አላልንም እያልን በተደጋጋሚ ለምንጠይቀው የማንነት ጥያቄ ሕጋዊ እውቅና ሊሰጠን ይገባል” የማይጠብሪ ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች

24

ደባርቅ: ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የማይጠብሪ ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች “ለማንነቴ እሮጣለሁ” በሚል የሩጫ ውድድር አካሂደዋል። ነዋሪዎቹ ባካሄዱት የማንነት የሩጫ ውድድር “ደንበራችን ተከዜ ነው፤ አማራ ነን እንጅ አማራ እንሁን አላልንም” ሥለኾነም መንግሥት ለምንጠይቀው የአማራነት ማንነት ጥያቄ ሕጋዊ እውቅና ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።

የትግራይ ሕዝብ ወንድማችን ነው ያሉት ነዋሪዎቹ በሰላም አብሮ መኖር ለሚፈልግ በራችን ክፍት ነው፤ ነገር ግን ለወንጀለኛ የሚኾን ቦታ የለንም ብለዋል።

ነዋሪዎቹ ጠለምት በጦርነት ውስጥ የነበረና በርካታ ውድመት የነበረበት መኾኑን አስታውሰው መንግሥት በጀት እንዲለቅላቸው፤ የወደሙ ተቋማት እንዲገነቡና በረሃብ ውስጥ የሚገኘው የአካባቢው ነዋሪ ሰብአዊ አርዳታ እንዲደርሰው ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ አቅርበዋል።

ለማንነቴ እሮጣለሁ በሚል በተካሄደው የሩጫ ውድድር በርካታ የከተማው ነዋሪዎች፣ የዞንና የከተማ አሥተዳደሩ የመንግሥት አመራሮች ተሳትፈውበታል።

የሩጫ መርኃ ግብሩ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ በውጭ የሚኖሩ የጠለምት ተወላጆች በገንዘብ በመደገፍ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምሥጋና ቀርቧል።

በውድድሩ ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡ ሯጮች ሽልማት ተበርክቷል።

ዘጋቢ :-አድኖ ማርቆስ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሐምሌ 10 /2015 ዓ.ም ለሚካሄደው የአረንጎዴ አሻራ ልማት መርሐ ግብር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁን የምዕራብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
Next articleበብቸና ከተማ አሥተዳደር ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጪ የተገነቡ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።