
ፍኖተ ሰላም: ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ነገን ዛሬ እንትከል”በሚል መሪ መልዕክት ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዝግጅቱ መጠናቀቁን የዞኑ ግብርና መምሪያ ኀላፊ ጥላሁን አለምነህ ለአሚኮ ገልጸዋል።
የዞኑ ግብርና መምሪያ ኀላፊ ጥላሁን አለምነህ እንደገለጹት፦
🌱 በአንድ ጀንበር የሚተከል 29 ነጥብ 9 ሚሊዮን ችግኝ ተዘጋጅቷል
🌱 2 ሺህ 991ሄክታር መሬት ለተከላ ተለይቷል
🌱 30 ሚሊዮን የሚጠጋ የችግኝ ጉድጓድ ተዘጋጅቷል
🌱 ለችግኝ ተከላዉ ከ800 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍል ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል
🌱 በዞኑ በወረዳዎችና ከተማ አሥተዳደሮች በ397 ቀበሌ በ816 የተከላ ቦታ የአንድ ቀን ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ይከናወናል።
🌱 በዞኑ በተያዘው የክረምት ወቅት በጠቅላላው 206 ሚሊዮን የሚጠጋ የደንና ፍራፍሬ ችግኝ ለመትከል መታቀዱን የዞኑ ግብርና መምሪያ ለአሚኮ አስታውቋል።
ዘጋቢ:- ዘመኑ ይርጋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!