
ባሕር ዳር: ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከጅቡቲ ወደብ አመራርና ይኸን ሥራ ከሚመሩት የሚንስቴር መስሪያ ቤት ተወካዮች ጋር በቀን 127 ሺህ 679 ወይም 12 ሺህ 767.9 ቶን ኩንታል የአፈር ማዳበርያ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ መኾኑን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ገልጿል።
እስከአሁን 9 ሚሊዮን 160 ሺህ 354 ኩንታል ወይም 916 ሺህ 035.4 ቶን ሀገር ውስጥ የገባ ሲሆን ጅቡቲ ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥም 89 በመቶው ሀገር ውስጥ ገብቶ ተሰራጭቷል።
አሁን ጅቡቲ ደርሶ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ያለው 1 ሚሊዮን 114 ሺህ 966 ኩንታል ወይም 111 ሺህ 496.6 ሜትርክ ቶን ሲሆን በአጭር ጊዜ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ ሌሊትና ቀን እየተሰራ መሆኑን የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል።
በቀሪ 15 ቀናት ውስጥም ሰባት መርከቦችን ወደ ጅቡቲ እንዲደርሱ በማድረግ ሀገር ውስጥ ለማስገባት አስፈላጊ የትራንስፖርት እና ሎጄስቲክስ ሥራ ተጠናቋል ተብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!