
ደብረማርቆስ : ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ኅላፊ አበበ መኮንን “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም ለሚካሄደው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዝግጅት መጠናቀቁን ለአሚኮ ተናግረዋል።
እንደ ዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ኅላፊ ገለጻ፦
🌳 በአንድ ጀንበር የሚተከሉ 33 ነጥብ 18 ሚሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል፡፡
🌳 319 ሄክታር መሬት ለተከላ ተለይቷል።
🌳 33 ሚሊዮን የችግኝ ጉድጓድ ተዘጋጅቷል።
🌳 ለችግኝ ተከላዉ ከ660 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍል ይሳተፋል።
🌳 በዞኑ በከተማ እና በገጠር የሚኖረዉ ማኅበረብ እና ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ።
🌳 በዞኑ በተያዘው የክረምት ወቅት 252 ሚሊዮን 119 ሺህ ችግኝ ለመትከል ታቅዷል።
🌳 እስካሁን ባለው ጊዜም በዞኑ በ17 ወረዳዎች በ318 ቀበሌዎች በ2 ሺህ 356 የተከላ ቦታ 6 ሺህ 771 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል።
🌳 በዞኑ በ2014 ዓ.ም ከተተከለው 277 ሚሊዮን ችግኝ 80 በመቶ የሚሆነው መጽደቅ ችሏል።
ዘጋቢ፦ ንጉስ ድረስ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!