“ዓላማችን ሪከርዳችንን መስበር ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

62

ባሕር ዳር: ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዳይ ኢትዮጵያን የመጠበቅ፣ የማክበርና የማበልጸግ ታሪክን የመቀየር እና ለትውልድ የመትረፍ ጉዳይ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ከማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ተግባራት ነጻ የሆነ ቀን የመረጥነው ይህ ቀን ሊያልፈው የሚገባ ኢትዮጵያዊ ስለሌለ ነው።

ሰኞን ስንመርጥ የሥራ መጀመሪያችንን ተፈጥሮን በመታደግ እንድንጀምር ነው ብለዋል።

“ፉክክራችን ከራሳችን ጋር ነው። ክልሎች፣ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና መንደሮች ከአምናው የበለጠ በመትከል የየራሳቸውን ሪከርድ እንደሚሰብሩ እናምናለን ሲሉ ገልጸዋል።

እያንዳንዳችንም የየራሳችንን ሪከርድ መስበር አለብንም ሲሉ አሳስበዋል።

“ችግር የራሱን ሪከርድ እንዲሰብር ልንፈቅድለት አይገባም። ችግር የራሱን ሪከርድ ከሰበረ ተሸንፈናል ማለት ነው።

ችግርን የምናሸንፈው መጀመሪያ የራሳችንን ፣ ቀጥሎ የአካባቢያችንን፤ በመጨረሻም የዓለምን ሪከርድ ስንሰብር መኾኑን አንስተዋል።

“እኔ ነገ በተደጋጋሚ ለመትከል ተዘጋጅቻለሁ። እናንተስ?

ነገ ሐምሌ 10 ቀን 2015 የራሳችሁን ሪከርድ በብዙ መጠን እስክትሰባብሩ ድረስ ዛፎችን ለመትከል ተዘጋጁ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ፖሊስ ኮሌጅ የመደበኛ ፖሊስ አባላትን እያስመረቀ ነው።
Next article“ልዩ ድጋፍ የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር የምክር ቤት አባላት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት ይጠበቅባቸዋል” አፈጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ