በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እየተከናወነ ነው።

147

አዲስ አበባ: ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ሐምሌ 9/2015 ዓ.ም የሚሾሙ ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት ሢመት እየተከናወነ ነው።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር)፣ የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሁም የተለየዩ የሃይማኖት አባቶች እና ምእመናኑ በተገኙበት በመንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እየተካሄደ ይገኛል።

ሲመቱ ለዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ነው እየተከናወነ ያለው በዚህም መሠረት የኤጲስ ቆጶሳቱ ስያሜና የተመደቡባቸው አህጉረ ስብከት፦

1. አባ ክንፈገብርኤል ተ/ማርያም ብፁዕ አቡነ ገሪማ፦ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀ/ስብከት

2. አባ ሣህለማርያም ቶላ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፦ የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት

3. አባ ስብሐት ለአብ ኃይለማርያም ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፦ ዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት

4. አባ አምደሚካኤል ኃይሌ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፦ ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት

5. አባ ኃይለማርያም ጌታቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ፦ ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት

6. አባ ጥላሁን ወርቁ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፦ ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

7. አባ ዘተ/ሃይማኖት ገብሬ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፦ ሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት

8. አባ አስጢፋኖስ ገብሬ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፦ ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት

9. አባ ወ/ገብርኤል አበበ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ፦ ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት

ዘጋቢ፦ ኤልሳ ግኡሽ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአቶ ግርማ የሺጥላ የሃውልት ምረቃ ፕሮግራም ተካሔደ።
Next articleየኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ።