
ባሕር ዳር: ሐምሌ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሊሰጣት መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ.ር) ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም እንደሚያስመርቅ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ በዕለቱ ለተወዳጇ አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጣት ተናግረዋል።
ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ሁለገቧ አርቲስት ጂጂ፣ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነጥበብ የአዊን ሕዝብ ቋንቋ እና ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ የክብር ዶክትሬቱ እንደሚበረከትላት ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት።
መረጃው የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!