የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ ኢንቨስትመንት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ሲያትል ገቡ፡፡

196

ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 07/2012ዓ.ም (አብመድ) በአቶ ዮሐንስ ቧያለው የተመራው የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ሲያትል ታኮማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

በሲያትል ከአማራ ምሁራን፣ ባለሀብቶች፣ ሲቪክ ማኅበራት እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለሚካሄደው ዝግጅት የኮሚቴ አባላት ናቸው ለሥራ ኃላፊዎቹ አቀባበል ያደረጉላቸው።

በቆይታቸውም በክልሉ ኢንቨስትመንት፣ በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ድጋፍ ፣ በወቅታዊ የክልሉ እና የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡ ሕዝባዊ ምክክሩም ከሁለት ቀናት በኋላ ይካሄዳል። ከዚህ ውይይት አስቀድሞ ነገ ጠዋት ከአማራ ተወላጅ ባለሀብቶች፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የማኅበረሰብ አንቂዎች ጋር በየዘርፉ ይወያያሉ።

የሥራ ኃላፊዎቹ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው፣ በአትላንታ፣ ኮሎምበስ፣ በዴንቨር፣ በሚኒሶታ እና በሳንሆዜ ከሰሞኑ መወያዬታቸው ይታወሳል።

ዘጋቢ፡- አስማማው በቀለ- ከሲያትል

ፎቶ፦ በአቻምየለህ ሙላት

Previous articleአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት 25ኛ የብር ኢዮቤልዩ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው፡፡
Next articleለሠራተኞች በሚከፈል ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማነስ ምክንያት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ሊዘጋ እንደሚችል ተገለጸ፡፡