
ባሕር ዳር: ሐምሌ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የ2015 በጀት ዓመት 4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ ጉባኤውን ከሐምሌ 07- 08 /2015 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ ቆይቶ አቶ መንበሩ ዘውዴ አስራትን የከተማዋ ከንቲባ አድርጎ በመሾም ተጠናቋል።
አቶ መንበሩ ዘውዴ አስራት በስራቸው ታታሪና በተሰማሩበት ሃላፊነት ሁሉ ውጤታማ የነበሩ፤ በአመራር ብስለታቸው የተመሰከረላቸው፤ ለሕዝብ የታመኑና በቅንነት የሚያገለግሉ አመራር እንደሆኑም በምክር ቤቱ ተነስቷል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪ በመሆን ሲያገለግሉ መቆየታቸውም ተገልጿል።
መረጃው የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!