በደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አሥተዳደር ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጪ የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን አስመረቀ ።

79

ደሴ: ሐምሌ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በመርሃ ግብሩ ላይ የጊምባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አህመድ ሙህየ በ13 ሚሊዮን ብር 6 ኪሜ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ፣ 100ሜትር የጌጠኛ ድንጋይ መንገድ ፣ 942 ሜትር የውሃ ማፋሰሻ ቦይ፣ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የመንገድ እና መብራት ግንባታ መከናወኑን ገልጸዋል።

የመሠረተ ልማት ሥራዎቹ ለሥራ እድል ፈጠራ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው የገለፁት ከንቲባው ወጣቶች ፕሮጀክቶቹን በመገንባት ተጠቃሚ መኾናቸውን ነው የተናገሩት ።

የደቡብ ወሎ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሃና አለባቸው ማኅበረሰቡን ያሳተፉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ነው የገለጹት ።

የዞኑ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ መርከቡ ታረቀ በበኩላቸው በከተማዋ የተሠሩ መሠረተ ልማት ሥራዎች በጥራት መሠራታቸውን ገልጸው በበጀት እጥረት ያልተጠናቀቁ የውኃ ማፋሰሻ ቦዮችና ሌሎች ስራዎች በቀጣይ ማኅበረሰቡን በማሳተፍ መጠናቀቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

ዘጋቢ፦ከድር አሊ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኮሌጁ ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው ሥራ ለመፍጠር ዝግጁ እንደሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች ተናገሩ።
Next articleፕሬዝዳንቷ ተመራቂ ፖሊሶች ዜጎችን ያለአድልኦ እንዲያገለግሉ አደራ ሰጡ።