“የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱት 40 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን አልፈዋል” የትምህርት ሚኒስቴር

26

ባሕር ዳር: ሐምሌ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱት 40 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

150 ሺህ 184 ተማሪዎች በኦንላይን የተሰጠውን የመውጫ ፈተና መውዳቸው ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የመውጫ ፈተና አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ 61 ሺህ 54 እጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን አልፈዋል። በዚህም 40 ነጥብ 65 በመቶ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡

እንደ ዶክተር ሳሙኤል ገለጻ 150 ሺህ 184 ተማሪዎች በኦንላይን የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ወስደዋል።

በአጠቃላይ ካለፋት 61 ሺህ 54 ተማሪዎች ውስጥ 48 ሺህ 632 ከመንግሥት ተቋማት መሆናቸውን ጠቅሰው 12 ሺህ 422 ተማሪዎች ከግል ተቋማት መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከተፈተኑት ተማሪዎች ውስጥ 62 ነጥብ 37 በመቶ ከመንግሥት ተቋማት ያለፋ ሲሆን 17 ነጥብ 2 ከግል ተቋማት ማለፋቸውን አብራርተዋል።

ፈተናው በ215 ኘሮግራም መሰጠቱን ጠቅሰው ውጤት በተመለከተ ለተቋማት መላክ መጀመሩን ጠቁመዋል።

የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች በተመለከተ ጥር ላይ ፈተና እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ዕጩ ተመራቂዎች ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተናውን ከሰኔ 30 ጀምሮ ላለፋት ስድስት ቀናት መውሰዳቸው ይታወሳል። ኢፕድ እንደዘገበው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ትልቁ አቅማችን ትብብራችን ነው” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
Next article“እስካሁን ድረስ ዝናብ ያላገኙ ቀበሌዎች አሉ” የምሥራቅ በለሳ ወረዳ