
ባሕር ዳር: ሐምሌ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ክልል አቀፍ የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻያ ሕዝባዊ ንቅናቄ በባሕርዳር ከተማ እያካሄደ ነው። ቢሮ ኀላፊው ማተብ ታፈረ (ዶ.ር) የትምህርት ሥርዓትን ማዘመን ሀገርን ለማዘመን ቁልፉ ተግባር ነው ብለዋል።
በአማራ ክልል በርካታ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች በመኾናቸው የመማር ማስተማርን ተግባር የሚጎዱ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል። ሀገርን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ እና ለማዘመን የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልና ዘመናዊነትን የተላበሰ ትውልድ መፍጠር ግድ እንደሚል ዶክተር ማተብ ተናግረዋል።
የትምሕርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር ሳይኾን የሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች ርብርብ የሚጠይቅ ስለመኾኑም በመድረኩ ተናግረዋል።
“ሀገር እና ሕዝቡን የሚወድ ሁሉ ለትውልድ ምንጭ የኾኑ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ይነሳ” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። ይህ ካልሆነ ግን እስካሁን የነበረን የትምህርት ጉዟችን የምንፈልገውን አይነት ትውልድ ለማግኘት አያስችለንም” ሲሉም ገልጸዋል
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!