የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የአፍሪካውያን የስኬታማዎች ሽልማት (African Achievers Award) አሸናፊ ሆኑ፡፡

47

ባሕር ዳር: ሐምሌ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ13ተኛው ዓመታዊ የአፍሪካ አሸናፊዎች ሽልማት የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እንግሊዝ ለንደን ውስጥ በተካሄደው የአፍሪካውያን የስኬታማዎች ሽልማት (African Achievers Award) አሸናፊ ሆኑ ።

ሽልማቱ ኢጋድ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ላደረገው አስተዋፅኦ መሆኑንም ተገልጿል።

ይህ ሽልማት ለስኬታማ ተግባር የተሰጠ ዕውቅና መሆኑን ሸላሚ ድርጀቱ አስታውቋል ።

ከብዙ የኢጋድ ስኬቶች ውስጥ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲሳካ የተደረገው ጥረት የሚጠቀስ መሆኑም ተመላክቷል ።

የአፍሪካ አሸናፊዎች ሽልማት ለአህጉሪቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለሚያደርጉ አፍሪካ ውስጥ ላሉ ታዋቂ ግለሰቦችና ድርጅቶች እውቅና በመስጠት እና በማክበር የአፍሪካን የላቀ ደረጃ የሚያከብር ዓመታዊ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ነው።

ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ትናንት ሐምሌ 7 ቀን 2015 ምሽት በተከናወነ የእውቅና ስነ-ስርዓት ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመገናኛ ብዙሃን መሪዎች ፣ባለሙያዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች በጉለሌ የእጽዋት ማዕከል የችግኝ ተካላ አካሄዱ።
Next article“ከአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጎን ለጎን ከሀገራት ልዑካን ጋር ስኬታማ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረግ ተችሏል” አቶ ደመቀ መኮንን