
ባሕር ዳር: ሐምሌ 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና የጀርመን ልማት ባንክ የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ክርስቶፍ ቲስኬንስ ተፈራርመውታል።
ስምምነቱ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በምስራቅ ጎጃም እና በአርሲ ዞኖች በግብርናው ዘርፍ ወሳኝ የሆኑ የገጠር እሴት ሰንሰለት መሻሻልን ለመደገፍ ያለመ ነው ተብሏል።
“የገጠር እሴት ሰንሰለትን በኢትዮጵያ ማጠናከር” በሚል መሪ ቃል የተያዘው ይህ ፕሮጀክት የአየር ንብረትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የግብርና ምርታማነት ለማረጋገጥ የሚውል መሆኑንም ነው የተገለፀው።
ፕሮጀክቱ በባለሙያዎች በተለዩ እና ከፍተኛ የዝናብ ጥገኝነት ባለባቸው አካባቢዎች ስነ-ምህዳራዊ ዘላቂነት ያለው እና የገበያ ተደራሽነትን ለማስፋት የሚያግዝ መሆኑ ተጠቅሷል።
ፕሮጀክቱ በዝናብ ላይ የተመሰረተ የግብርና ልማትን በተለይም የእህል እና ጥራጥሬ ምርትን የአርሶአደሩን የግብአት አቅርቦትን ማሻሻል ላይ ያተኮረ እንደሆነም የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!