አቶ ደመቀ መኮንን ከጋምቢያና ማላዊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ።

25

ባሕር ዳር: ሐምሌ 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጋምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማመዱ ታንጋራ (ዶ/ር) እና ከማላዊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናንሲ ቴምቦ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በኬንያ እየተካሄደ ከሚገኘው 43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሔደ ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ከጋምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማመዱ ታንጋራ (ዶ/ር) እንዲሁም ከማላዊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናንሲ ቴምቦ ጋር ባደረጉት ውይይት በሀገራቱ መካከል የሁለትዮሽና ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በሀገራቱ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መስማማታቸው ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ እና የቱርክ ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ።
Next article“መምህራን የሀገር ግንባታ እና የትውልድ ብርሃን መሰረቶች ናቸው” ማተብ ታፈረ (ዶ.ር)