
ባሕር ዳር: ሐምሌ 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በግብጽ ካይሮ ተገናኘተው መምከራቸው ተገለጸ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ፕሬዝዳንት ኢሳይስ አፈወርቂ በሱዳን ቀውስ እና ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
ሁለቱ መሪዎች የኢትዮጵያና የኤርትራን ቀጣይ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የትዊተር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራን ጨምሮ የሱዳን ጎረቤት ሀገራት በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በካይሮ ተገናኝተው መምከራቸው ይታወቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!