“ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ላላት ግንኙነት የበለጠ ትኩረት እና ዋጋ ትሰጣለች” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

44

ባሕር ዳር: ሐምሌ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ላላት ግንኙነት የበለጠ ትኩረት እና ዋጋ እንደምትሰጥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

አቶ ደመቀ በ43ኛው የአፍሪካ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ለመሳተፍ ዛሬ ኬንያ ናይሮቢ መግባታቸው ይታወቃል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከስብስባው በፊት ከካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጄዩን ምቤላ ምቤላ ጋር በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን እና በሁለቱ ሀገሮች የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ውይይት አካሄደዋል።

በውይይቱ ላይ የፖለቲካ ምክክር እና በባለብዙ ወገን መድረክ እና በሌሎች ጉዳዬች በጋራ አብሮ መስራት ስለሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ያተኮረ ምክክር በቅርቡ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

አቶ ደመቀ ከአፍሪካ አገራት ጋር ለሚኖረን ግንኘነት የበለጠ ትኩረት እና ዋጋ እንሰጣለን ብለዋል።

ስለ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እና አፈጻጸም እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ለመፍታት መንግስት በመርህ ላይ ተመስርቶ ያሳለፋቸው ውሳኔዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ካሜሮን በዓለም አቀፍ መድረክ ላደረገችው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

43ኛው የአፍሪካ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል የቆየውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በኢንቨስትመንት ትስስር እናጠናክራለን” የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በካይሮ ተወያዩ።