
ባሕር ዳር: ሐምሌ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንዱትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የንግድና ኢንዱትሪ ሚኒስትር ጋር የሁለቱን ሀገራት የኢንቨስትመንት ትስስር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት ማድረግ የሚፈልጉ ባለሃብቶችና በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማለትም በኬሚካል፣ በአውቶሞቲቭ በግብርና ምርቶችና ግብአቶች ቴክኖሎጂ ላይ መሰማራት ፍላጎቱ ያላቸው ኢንዱስትሪዎች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል የኢንቨስትመንት ትስስሩ አናሳ መኾኑን የገለጹት የኢንዱትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በሀገራቱ መካከል የዘለቀውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በኢንቨስትመት እናጠናክራለን ብለዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት የኢንቨስትመትን ትስስር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ በሩሲያ በኩልም ጉዳዩን በሚመለከት ለሁሉም የሥራ ኀላፊዎች አስፈላጊው ተልእኮ መሰጠቱን እና እ.ኤ.አ በ2023 መጨረሻም የንግድና ኢንቨስትመነት ተወካዮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልኩ ቃል መግባታውን ጠቁመዋል፡፡
ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የኢንቨስትመንት ትስሰሩን ለማጠናከር በኢትዮጵያ በኩል የተወሰደው ተነሳሽነትም የሚያበረታታ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!