
ባሕር ዳር: ሐምሌ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የቢሯቸውን የ2015 በጀት ዓመት የ11 ወር እቅድ አፈጻጸም ለክልሉ ምክር ቤት የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አቅርበዋል፡፡
በሪፖርታቸውም ሚዲያ ጠንካራ የተግባቦት ሥራን ለመሥራት ሁነኛ መሣሪያ መኾኑን አንስተው በዓለም አቀፍም ሆነ ሀገር አቀፍ እና በክልል የሚንቀሳቀሱ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ማስፋትና የጋራ መግባባት እንዲፈጠር መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ከተግባቦት ሥራዎች አንጻር መረጃዎችን የመስጠት፤ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በሚፈለገው መጠን አለመጠቀም ይስተዋላል ያሉት ኃላፊው ከመዋቅሩም ባሻገር በአመራር ደረጃም ጭምር ሕዝብና መንግሥትን ማቀራረብ እና ማገናኘት የሚያስችል ገንቢ የተግባቦት ሥራዎችን መሥራት ይገባናል ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!