አቶ ደመቀ መኮንን በአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ገቡ።

74

ባሕር ዳር: ሐምሌ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ43ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጀሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፥ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ባጫ ደበሌን ጨምሮ ሌሎች የኬንያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ስብሰባው “የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ ከሐምሌ 6 እስከ 8 ቀን 2015 ድረስ ይካሄዳል።

በስብሰባው ላይ የኅብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የሕብረቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ቀጣናዊ የአፍሪካ ተቋማት ኃላፊዎች እና እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዘገበው ኢዜአ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበዞኑ ከ1ሺህ 700 በላይ ለኾኑ አረጋውያንና በኢኮኖሚ አቅማቸው ደካማ ለኾኑ ግለሰቦች ቤታቸው በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕድሳትና ግንባታ ሊደረግላቸው ነው፡፡
Next articleቆቦ ከነማ እና ጣና ክፍለ ከተማ ለፍፃሜ ደረሱ።