
ባሕር ዳር: ሐምሌ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የግብርና ሚኒስቴር የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል በግብዓት አቅርቦት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ የግብርና ሥራዎችን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት በግብርና ሚኒስቴር የኢንቨስትመንት አና የግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሶፊያ ካሳ እንደገለጹት፣ እስካሁን 9.6 ሚሊዮን የአፈር ማዳበሪያ በመሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል ለአርሶ አደሩ ደርሷል።
የአርሶ አደሩ የማዳበሪያ ፍላጎት አሁንም ያልተመለሰ በመሆኑ ተጨማሪ የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገቡ የገለጹት ሚኒስትር ዴዔታዋ፣ ከሶስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር እንደሚገባም አስታውቀዋል።
የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን መጠቀም ሌላኛው አማራጭ በመሆኑ አርሶ አደሩ በአማራጭነት እንድጠቀም ወ/ሮ ሶፊያ ጠቁመዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!