ትናንት ምሽት በሀገሪቱ በረካታ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦቱ ወደነበረበት ተመልሷል።

46

ባሕር ዳር: ሐምሌ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በበረካታ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦቱ ወደነበረበት ተመልሷል፡፡

ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት የተመለሰው በማመንጫ ጣቢያው ላይ ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር ለማስተካከል በተደረገ ከፍተኛ ጥረት ነው፡፡

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ በትግዕስት ለተጠባበቃችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት።

በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በበረካታ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ነጻነት ተፈጥሯዊ መብት ነው፤ የተነጠቅነውም ያስመለስነውም ተፈጥሯዊ መብታችንን ነው” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
Next articleሶስት ሚሊዮን ተጨማሪ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።