በአማራ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ከአስፈጻሚ አካላት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።

45

ባሕር ዳር: ሐምሌ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ከአስፈጻሚ አካላት ጋር በ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ተከታታይ ውይይቶች እያደረጉ ነው።

በዛሬው ዕለትም የግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ውኃ ሀብት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከተጠሪ አስፈጻሚ አካላት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።

በውይይቱ ላይ ግብርና ቢሮ፣ መሬት ቢሮ፣ ውኃና ኢነርጅ ቢሮ፣ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ እና አካባቢ ጥበቃና ደን ልማት ባለሥልጣን የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለቋሚ ኮሚቴው ያቀርባሉ።

ቋሚ ኮሚቴው የአስፈጻሚ አካላትን የሥራ አፈጻጸም ካዳመጠ በኃላ ጥንካሬ እና ጉድለቶችን የሚጠቁም ግብረ መልስ እንደሚሠጥም ይጠበቃል። የአስፈጻሚ አካላትን ዋና ዋና የሥራ አፈጻጸም እና የቋሚ ኮሚቴውን ግብረ መልስ አሚኮ ኦንላይን ለተከታታዮቹ በቀጣይነት የሚያደርስ ይኾናል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሐረር ከተማ የዓለም የቅርስ ከተሞች አባል ኾነች።
Next article“ከተሞቻችን የነጻነት ብቻ ሳይኾን በራስ አቅም የመልማትም ተምሳሌት ኾነዋል” የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ