
ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 06/2012ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛው የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ እርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበበ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡
በሻምፒዮናው ከ28 ቡድኖችና ተቋማት የተውጣጡ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
በውድድሩ የመክፈቻ ዕለት የአሎሎ ውርወራ ማጣሪያና ፍፃሜ፣ የስሉስ ዝላይ ማጣሪያና ፍፃሜ፣ እንዲሁም ከ100 ሜትር እስከ 800 ሜትር የማጣሪያ ውድድሮች እንደሚካሄዱ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡-የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን