በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ በአንድ ጀምበር ሦስት ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርኃ ግብር ተካሄደ።

60

ጎንደር: ሐምሌ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በተያዘው ዓመት በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ከ15 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለተከላ የተዘጋጀ ሲኾን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከተጀመረበት ከ2011 እስከ 2014 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በ105 ተፋሰሶች የአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራ ሲሠራ ቆይቷል።

ያለፈው ዓመት 13 ሚሊዮን ችግኝ የተተከለ ሲኾን የመጽደቅ ምጣኔውም ከ75 በመቶ በላይ መኾኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ወርቁ ኃይለማርያም ገልጸዋል።

በችግኝ መትከል መርኃ ግብሩ የተሳተፋት የስሁር ሳር ውኃ ቀበሌ አርሶ አደሮችም ከዚህ ቀደም በችግኝ ተከላ መርኃ ግብር ሲሳተፉ መቆየታቸውን አስረድተዋል።

በዚህም የአፈር ክለትን መከላከል መቻሉን፤ በንብ ማነብ ተጠቃሚ መኾናቸውን እና ለከብቶችም መኖ በማግኘት ላይ መኾናቸውን ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ዳንኤል ወርቄ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተገባደደው በጀት ዓመት 125 የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ።
Next articleአስፈፃሚ አካላት ጠንካራ ሥራዎችን የበለጠ በማጠናከር ደካማ ጎኖቻቸውን እየፈቱ እንዲሄዱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላት አሳሰቡ።