የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተገባደደው በጀት ዓመት 125 የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ።

70

ባሕር ዳር: ሐምሌ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በተቋሙ የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት እንደገለጸው፥ አገልግሎቱ በ2015 በጀት ዓመት 160 የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ 125 ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አድርጓል።

በዚህም 45 ሺህ 828 ደንበኞች የኃይል ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከተሞቹን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ 1 ሺህ 891 ነጥብ 14 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እንዲሁም 1 ሺህ 236 ነጥብ 58 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ እና የ405 ትራንስፎርመሮች ተከላ ሥራ ተከናውኗል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጤናው ዘርፍ የዲጅታል ክፍያ ሥርዓትን ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ ነው።
Next articleበማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ በአንድ ጀምበር ሦስት ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርኃ ግብር ተካሄደ።