ውሜን ኢምፓወርመንት አክሽን ከሄልቪተስ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለደቡብ ወሎ ዞን እና ለደሴ ከተማ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

60

ባሕር ዳር: ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ድጋፉ ኮምፒውተርና የሞተር ሳይክል ተሽከርካሪ ሲኾን በገንዘብ ሲተምን ከ1ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ መኾኑም ተጠቅሷል፡፡

የውሜን ኢምፓወርመንት አክሽን የፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ኃይለማርያም ሽፈራው እንዳሉት ፕሮጀክቱ ከተመረጡ ወረዳዎች ጋር በጋራ ይሠራል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው የሥራ ግንኙነት በወረዳም ኾነ በከተማ አሥተዳደር ምክር ቤቶች የተሽከርካሪ እጥረት መኖሩን ተገንዝበናል ብለዋል፡፡ ችግሩን በመመልከታቸውም ሞተር ሳይክልና ኮምፒውተር በመደገፍ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
ለደሴ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 1 ሞተር ሳይክልና አንድ ኮምፒውር ለደቡብ ወሎ ዞን አምስት ወረዳ አሥተዳደር ምክር ቤቶች አንድ አንድ በድምሩ 6 ሞተርና ስድስት ኮምፒውተር መደገፋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል የደሴ ከተማ አሥተዳር ደሴ ዙሪያ ወረዳና የወረባቦ ወረዳ አሥተዳደር ምክር ቤት መሪዎች የተደረገው ድጋፍ ቀበሌዎችን ተንቀሳቅሶ ለመደገፍና ክትትል ለማደረግ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡ ለድጋፉም አመስግነዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀን አምባቸው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሕዝብ የሚያነሳቸውን የአገልግሎት አሠጣጥ ችግሮች ለመቅረፍ እየሠራን ነው” የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን
Next articleቺርቤዋ ሴኒ 30 ጌርክ 2015 ምሬት አሜታ