
ባሕር ዳር: ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢፌድሪ ገንዘብ ሚኒስተር ሚኒስትር አህመድ ሽዴ እና በባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) የሚመራው የፌደራል ፣የክልልና የከተማ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በባሕር ዳር ከተማ ያለውን የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
ልዑኩ በከተማ አስተዳደሩም ሆነ በአለም ባንክ በጀት እየተገነቡ ያሉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችንና በግለሠቦች እየተሠሩ ያሉ “የሌማት ቱሩፋት” ሥራዎችን ማለትም የበሬ ማድለብ ፣የዶሮ እርባታ እና እንቁላል ምርት ፣የወተት ልማት ፣የማርና መሰል የእንስሳት ሀብት ልማቶችን ተመልክተዋል።
የከተማ አሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ እንደሚያሳየው ልዑኩ በጉብኝቱ በከተማው ኢንዱስትሪ መንደር ካሉ ፋብርካዎች መካከል የጌታሰው አያሌው ቶፕ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ፣የሻምበል መንገሻ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ ፣ ሙሌ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ ፋብርካ ፣የቢአይካ የግራናይትና እምነ-በረድ ፋብሪካዎችን የሥራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችንና የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸውን ሠራተኞች የማበረታታት ተግባር አከናውነዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
